ሕፃናት እና አዳጊያን
ቅድስት ቤተክርስቲያንትኩረት ሰጥታ ከምትሰራባቸው ሥራዎች አንዱሕፃናት ቋንቋቸውን ባህላቸውን እንዲያውቁ ሃይማኖታቸውን ጠብቀው የነገይቱን ቤተ ክርስቲያን ብቁ ሆነው እንዲረከቡ ማድረግ ነው። ይህንን ቅዱስ ሥራም የዴንቨር ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክም አጽንኦት በመስጠት በሰንበት ትምህርት ቤቱ ሥር የሕፃናት ክፍል በማቋቋም የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል።ሕፃናቱም ፊደል ከመቁጠር አንስቶ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፤ግብረገብ እየተማሩ ሲሆን የሚሰጣቸውን ትምህርት በብቃት እንዲከታተሉም በዕድሜአቸው በመከፋፈል የተለያዩ ክፍሎች ያሉ ሲሆን በእነዚህም ክፍሎች ሰንበት ትምህርት ቤቱ የመደባቸው እና በበጎ ፈቃድ የሚያገለግሉ ምእመናን ይገኙበታል።


Play »