በአሕዛብ መካከል ብዘራቸው እንኳን በሩቅ አገር ሳሉ ያስቡኛል ት/ዘካ ፲፥፰

ቤተክርስትያናችን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማዋን፣ቀኖናዋንና ትዉፊቷን ጠብቃ፥ ላለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት ትምህርተ ወንጌልን በማስፋፋት፣ ምዕመናንን በማብዛት፣ ታሪክን በመጠበቅና በመንከባከብ ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለዓለም ታላቅ አስተዋፅዖ አበርክታለች።

የሰበካ ጉባኤ

የደብሩ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ ቤት አባላት እና የአጥቢያው ምእመናን ጉባኤ ነው። ይህ ጉባኤ የአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ የመጨረሻ ወሳኝ አካል ነው።

ዓላማችን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ሥርዓትና ትውፊት መሠ ረት ትምህርተ ወንጌልን ለሁሉ ማዳረስ፣ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከአጽራረ ቤተክርስቲያን መጠበቅ፤  በውጭው ዓለም የሚኖረው ሕዝብ ሃይማኖቱን ፣ ሥርዓቱን ፣ ትውፊቱን፣ ባሕሉንና ቋንቋውን ጠብቆ እንዲኖር ተግቶ ማስተማር፤ አዳዲስ አማንያንንም አስተምሮ አጥምቆ መቀበል፤ የቤተክርስቲያን ዶግማ፣ቀኖናና ትውፊት ሳይበረዝ ከአባቶቻችን በተረከብነው መልኩ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ።

የቤተክርስትያን ዜናዎች

የቤተክርስትያን ካላንደር

ወቅታዊ ስብከቶች

ቀጣዩ ክፍለዝዜ የሚጀምረው

0Weeks0Days0Hours0Minutes0Seconds